የቀድሞ የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር እና አሁን በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ውስጥ በአባልነት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ እስክንድር ነጋ ንቅናቄያቸው ከመላ አባላቱ እውቅና ውጪ ከሌሎች ኃይሎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር መሞከሩ ተቀባይነት የለውም አሉ።

ADDIS_NEWSneutral2026-08-24 19:21:42 UTC
AdYour ad here[email protected]

የቀድሞ የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር እና አሁን በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ውስጥ በአባልነት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ እስክንድር ነጋ ንቅናቄያቸው ከመላ አባላቱ እውቅና ውጪ ከሌሎች ኃይሎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር መሞከሩ ተቀባይነት የለውም አሉ። አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በአፋብን ውስጥ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያልተቀበሉት በውስጥ እና ረዣዥም ባሏቸው የውጭ ኃይሎች ጫና ምክንያት ከአመራርነት በመገፋቴ ነው ብለዋል። ከመንግስት ወታደራዊ ኃይሎች እና ለጊዜው ስማቸውን መጥቀስ ከማይፈልጉ ታጣቂዎችተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር የተናገሩት አቶ እስክንድር ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ወደ ትጥቅ ትግል በመግባታቸው ግን እንደማይቆጩ ተናግረዋል ። አቶ እስክንድር ነጋ ከጋዜጠኝነት ፣ እስከ ሰላማዊ የፖለቲካ መሪነት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]