በደቡባዊ ሱዳን በጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 27 ሰዎች ተገደሉ
በደቡባዊ ሱዳን በጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 27 ሰዎች ተገደሉ በደቡባዊ ሱዳን በጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 27 ሰዎች ሲገደሉ ከነዚህ አራቱ ህፃናት መሆናቸውን የሀገር ውስጥ የህክምና ቡድን አስታውቋል። በሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (SPLM-N) አማፂያን በደቡብ ኮርዶፋን የኦቶሮ ጐሳ አባላት በሚኖሩባቸው ቃርዱድ እና አቡ ሃማማ በተባሉ አካባቢዎች ባደረሷቸው ጥቃቶች ግድያው መፈጸሙን የጉዳተኞችን ቁጥር የሚከታተለው የሱዳን ሀኪሞች መረብ አስታውቋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በ SPLM-N እና በደቡብ ኮርዶፋን ኑባ ተራሮች ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ባለው የኦቶሮ ጐሳ መካከል ብርቱ ውጊያ ተቀስቅሶ እንደነበር ዘገባው አመልክቷል። በመሬት ይገባኛል ሰበብ የተቀሰቀሰው አዲሱ የጎሳ ግጭት በሀገሪቱ በብሄራዊ ጦር ኃይሉ እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል እየተካሄደ ያለውን…
Read the full story at addis_news ↗