የቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ እና ረድኤቷ አይለየን🙏
የቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ እና ረድኤቷ አይለየን🙏 በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በግብጽ በስደቷ፣ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ከሙታን ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ለተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡…
Read the full story at addis_news ↗