በኑሮ ውድነት የተማረረውን ሕዝብ በቅናሽ ስንዴ አቀርባለሁ ብሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር የሰበሰበው 'ኢት ፓስ' አሁን ጥያቄ እየተነሳበት ነው።
በኑሮ ውድነት የተማረረውን ሕዝብ በቅናሽ ስንዴ አቀርባለሁ ብሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር የሰበሰበው 'ኢት ፓስ' አሁን ጥያቄ እየተነሳበት ነው። ባለቤቱ ወልደጊዮርጊስ ይልቃል፣ ድርጅቱ እንደ PLC ተመዝግቦ እያለ ግብር ለምን አይከፍልም ለተባለው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። 'ኑሮ ማረጋጋት ላይ ስለምሠራ ግብር አይመለከተኝም' ያሉት ወልደጊዮርጊስ፣ ውንጀላዎቹን በሙሉ ውድቅ አድርገዋል። በሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ጥርጣሬ ቢፈጠርም፣ እሳቸው ግን እስከ ሞት ድረስ በአቋማቸው እንደሚጸኑ ተናግረዋል። ይህ ጉዳይ ወዴት የሚያመራ ይመስላችኋል? ኮሜንት ላይ እንወያይ።"
Read the full story at addis_news ↗