የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-26 15:30:59 UTC
AdYour ad here[email protected]

የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሐመድ አሊ ዩሱፍ ከኢጋድ ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን ሰላም እና ደህነት ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ በሱዳን ሰላም ለማስፈን ጥረት ከሚያደርገው የሱዳን የሰላም ተልዕኮ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡ በውይይቱ በሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የህብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡ @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]