ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤን ልታስተናግድ ነው

ADDIS_NEWSneutral2026-08-27 10:30:09 UTC
AdYour ad here[email protected]

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤን ልታስተናግድ ነው ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ (APPS) ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደምታስተናግድ የአፍሪካን ገቨርነንስ ሴንተር (AGC) አስታወቀ። ጉባኤው ከመላው አህጉሪቱ የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እና የአስተዳደር ባለድርሻ አካላትን ያገናኛል። ጉባኤው «መልካም አስተዳደር ለዕድገት፦ ፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ መጻኢ እድል አርክቴክቶች» በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ የልማት አጋሮች፣ ምሁራን፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ የወጣት መሪዎች እና የግል ዘርፍ ተዋንያን ይሳተፋሉ ተብሏል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]