በኢሮብ ወረዳ 35 ሺህ ህዝብ ለከባድ ድርቅ ተጋልጧል።

ADDIS_NEWSneutral2026-08-27 14:55:19 UTC
AdYour ad here[email protected]

በኢሮብ ወረዳ 35 ሺህ ህዝብ ለከባድ ድርቅ ተጋልጧል። በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኘው ኢሮብ ወረዳ ከባድ ድርቅ እየተጋፈጠ ሲሆን፤ በአካባቢው የሚኖሩ 35 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለድርቅ አደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል። በወረዳው የክረምት ዝናብ በበቂ ሁኔታ ባለመዝነቡ የውሃ ጉድጓዶች መድረቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በውሃ እጥረቱም የቤት እንስሳት መሞት መጀመራቸውን አስረድተዋል። በወረዳው የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በከፍተኛ ተራራና ተዳፋት አካባቢዎች መሆናቸው የተጀመረውን የእርዳታ ማዳረስ ስራ ፈታኝ እንዳደረገው ተጠቁሟል። የአካባቢው አርሶ አደሮች እንደሚሉት፣ ከዚህ በፊት እንደ ዘንድሮ ያለ ከባድ ድርቅ አጋጥሟቸው አያውቅም። የዝናብ እጥረቱ በማሳ ላይ የተዘራው እህል እንዲደርቅ ከማድረጉም በላይ በክረምት ዝናብ ይሞሉ የነበሩ የውሃ ጉድጓዶች እንዲደርቁ አድርጓል። የኢሮብ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]