በንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራቹ  ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተጠንቀቁ ።

ADDIS_NEWSneutral2026-08-29 05:30:36 UTC
AdYour ad here[email protected]

በንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራቹ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተጠንቀቁ ። በ3 የሻይ ሲኒ ደረሰኝ ምክንያት 300 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል። በአዲሱ የታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ደረሰኝ አለመስጠት ንብረትዎን ሊያሳጣዎት ይችላል! አንድ ሰራተኛዎ ቸልተኛ ሆና 100 ብር ለሚያወጣ 'ሻይ' ደረሰኝ ባትቆርጥ... ቅጣቱ 100 ብር ሳይሆን 100 ሺህ ብር ነው ተብሏል። ይባስ ብሎ ደግሞ... ሰራተኛዋ ለ3 ደንበኞች ደረሰኝ ካልሰጠች፣ ለድርጅቱ ባለቤት የ300 ሺህ ብር መብረቅ የመሰለ ቅጣት ይወርድበታል። ይህ ቅጣት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 125 ንኡስ ቁጥር 2 መሰረት በባለስልጣኑ ሊነሳ ወይም 'ይቅር' ሊባል አይችልም! መፍትሄው መክፈል ብቻ ነው! ነጋዴዎች ተጠንቀቁ፣ ሰራተኞቻችሁን አስተምሩ።

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]