በአፍሪካ ዞን 5 የወጣቶች ጨዋታ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በአፍሪካ ዞን 5 የወጣቶች ጨዋታ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ቡድኑ በኬንያ የተደረገውን 2ኛው የአፍሪካ ዞን 5 የወጣቶች ጨዋታ ላይ አበረታች ውጤት ይዞ ተመልሷል፡፡ በውድድሩ በአራት የስፖርት አይነቶች በአትሌቲክስ ፣ በብስክሌት ፣ በውሃ ዋና እና በቅርጫት ኳስ ተሳትፋ በአጠቃላይ 12 ሜዳልያዎችን በማምጣት ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች፡፡ በውድድሩ ላይ ከተገኙት መካከል ስድስቱ የወርቅ ሜዳልያዎች ናቸው። ልዑኩ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ሲደርስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በቦሌ አየር ማረፊያ በመገኘት ለአትሌቶች የአበባ ጉንጉን ማበርከታቸውን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ዳናይት ሲሳይ
Read the full story at amharamassmedia ↗