320 ነጥብ ያመጡት ቄስ ሰይፉ ተስፋይ !

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-29 19:15:46 UTC
AdYour ad here[email protected]

320 ነጥብ ያመጡት ቄስ ሰይፉ ተስፋይ ! " ትምህርት ፍላጎትና ተነሳሽነት ካለ ዕድሜ አይገድበውም " የሚለውን እውነታ በተግባር ያሳዩት ቄስ ሰይፉ ተስፋይ፣ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 320 ነጥብ በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ከሚጠባበቁ ተፈታኞች መካከል ተጠቃሽ ሆነዋል። ቄስ ሰይፉ ተስፋይ በትግራይ ክልል፣ ደቡባዊ ዞን፣ ሰለዋ ወረዳ፣ ደጀን ቀበሌ፣ ግራዛፎ መንደር ነዋሪ ናቸው። የ66 ዕድሜ ባለፀጋው ቄስ ሰይፉ፣ በሰለዋ ከተማ በሚገኘው የአንበሳ ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ በመሆን እየሰሩ ነው። ከሥራቸው ጎን ለጎን ግን ትምህርታቸውን በመቀጠል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመፈተን ችለዋል። በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ 29 ሺህ ተፈታኞች መካከል ቄስ ሰይፉም አንዱ ሲሆኑ፣ 320 ነጥብ በማምጣት የማለፊያ ውጤት ካመጡ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]