አንዲት እናት በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በአንድ ጊዜ አራት ሴት ህፃናትን በሰላም ተገላገለች
አንዲት እናት በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በአንድ ጊዜ አራት ሴት ህፃናትን በሰላም ተገላገለች በጎፋ ዞን ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ተነገረ። በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገቢው ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ለተከታታይ አምስት ቀናት በቅርብ የሕክምና ክትትል ስር ቆይታ ወሊዱን ያከናወነችው እናት፣ በአሁኑ ወቅት ከነሙሉ ጤንነታቸው ከ አራቱም ህፃናት ጋር በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ግላንደ ጊሎ እንደገለጹት፣ በሆስፒታሉ ደረጃ ሁለት እና ሦስት ህፃናትን በአንድ ጊዜ ማዋለድ የተለመደ ቢሆንም፣ በአንድ ወሊድ አራት ህፃናትን በሰላም ማዋለድ መቻሉ በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያው ነው። የህፃናቱ አባት አቶ ናፍቆት ቡሼ በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደም የአምስት ሴት ልጆች አባት እንደነበሩ አጋልጠው፤…
Read the full story at addis_news ↗