የገቢዎች ሚኒስቴር የኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ የሆኑ የማምረቻ ተቋማት፣ በተለይም የቢራና የታሸጉ መጠጦች ፋብሪካዎች ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የክትትል ካሜራዎችን መግጠም መጀመሩ ካፒታል ጋዜጣ ዘገበ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-30 19:09:35 UTC
AdYour ad here[email protected]

የገቢዎች ሚኒስቴር የኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ የሆኑ የማምረቻ ተቋማት፣ በተለይም የቢራና የታሸጉ መጠጦች ፋብሪካዎች ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የክትትል ካሜራዎችን መግጠም መጀመሩ ካፒታል ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ መንግሥት ለዲጂታል የክትትል ሥርዓቱ ወደ 300 ሚሊዮን ብር የሚገመት በጀት መድቧል። ካሜራዎቹ የምርት መስመሮችን፣ የማሸጊያ ክፍሎችን፣ መጋዘኖችን፣ የጭነት መውጫዎችንና የምርት መጓጓዣን በቅጽበት ለመከታተል እንደሚውሉ ተገልጿል። ሥርዓቱም የፋብሪካዎች ትክክለኛ ምርት ከሚያሳውቁት የምርት መጠን ጋር ያለውን ልዩነት በመቆጣጠር የግብር ማምለጫን ለመቀነስ ያለመ ነው። በመመሪያዎቹ መሠረት አልኮል፣ ቢራ፣ ወይን፣ የታሸገ ውሃ፣ ትምባሆ፣ ሽቶ እና ጣፋጭ ወይም ካርቦኔትድ መጠጦችን ጨምሮ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ምርቶች በዲጂታል ኮድ ወይም በኤክሳይዝ ማህተም እንዲለዩ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]