የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች በ10ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ምሽት 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በመርሃ ግብሩ ምሽት 11 ሰዓት አራት ጨዋታዎች ሲደረጉ ቼልሲ ከሰንደርላንድ እንዲሁም ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት ብራይተን ከብረንትፎርድ እንዲሁም ኢፕስፒች ከቦርንማውዝ ጨዋታቸውን ያደርጋሉለ። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ደግሞ በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼሰተር ዩናይትድ አስቶንቪላን ያስተናግዳል፡፡ ሊጉን አርሰናል በ27 ነጥብ ሲመራ፤ የትላንት ጨዋታን ጨምሮ ሶስት ተከታታይ ሽንፈት ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ በ21፤ እንዲሁም የዛሬ ጨዋታ የሚቀረው ብራይተን በ19 ነጥብ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗