በበርካታ የወንጀል ድርጊቶች የሚፈለገው የሕንድ ወንበዴ በኢትዮጵያ ተገኘ
በበርካታ የወንጀል ድርጊቶች የሚፈለገው የሕንድ ወንበዴ በኢትዮጵያ ተገኘ በሕንድ ፑንጃብ ግዛት ውስጥ በቁጥር ከ35 በላይ በሆኑ ከባድ ወንጀሎች እና የግድያ ክሶች የሚፈለገው ጉርዊንደር የተባለ የወንበዴ ቡድን መሪ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ሀገሩ መባረሩ ተገለጸ። የሕንድ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ ከተጠርጣሪው ፍለጋ ጋር በተያያዘ «ኦፕሬሽን ሻሂድ» በሚል ስያሜ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ዘመቻ፣ ግለሰቡ ጥቅምት 27 ቀን በኢትዮጵያ ተይዞ ባለፈው እሁድ ማለዳ በኒው ዴሊ አየር ማረፊያ ሲደርስ በፑንጃብ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል። ከተለያዩ ሀገራት የሐሰት ፓስፖርቶችን በመጠቀም ሲዘዋወር የቆየውና የኢንተርፖል ቀይ ማስታወቂያ ወጥቶበት የነበረው ይህ ግለሰብ፣ ከሀገር ውጭ ሆኖ በፑንጃብ ውስጥ የግድያ እና የዝርፊያ ወንጀሎችን ሲመራ እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል። @Addis_News…
Read the full story at addis_news ↗