የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገባቸውን እስከ ህዳር 2 እንዲያቀርቡ የቅጣት ዕድል ሰጠ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገባቸውን እስከ ህዳር 2 እንዲያቀርቡ የቅጣት ዕድል ሰጠ የ2018 የግብር ዘመን ማሳወቂያ ጊዜ ዛሬ ጥቅምት 30 መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ቢሮው እስከ ረቡዕ ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን የሚቀርቡ የሂሳብ መዝገቦችን በቅጣት ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ አስታውቋል። ከህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሂሳብ መዝገብ ማቅረቢያው ሙሉ በሙሉ የሚዘጋ ሲሆን፣ ቢሮው ባለው መረጃ መሠረት ግምት በመስጠት ከከባድ ቅጣት ጋር ግብሩን እሰበስባለው ብሏል። ግብር ከፋዮች የተሰጣቸውን የሁለት ቀናት ተጨማሪ ዕድል በመጠቀም የሂሳብ መዝገባቸውን በኦንላይን እንዲያቀርቡ እና ያልተከፈሉ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗