«በሀዋሳ ከተማ የተባባሰው የቤት ኪራይ ዋጋ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ ተገለጸ»
«በሀዋሳ ከተማ የተባባሰው የቤት ኪራይ ዋጋ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ ተገለጸ» በሀዋሳ ከተማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መምጣቱ በተለይም በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ተጠቃሚዎች ላይ ከባድ የኑሮ ጫና መፍጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ። ቀደም ሲል በ4 ሺህ ብር ይከራዩ የነበሩ ትንንሽ ቤቶች አሁን ከ6 ሺህ እስከ 7 ሺህ ብር፣ ባለአንድ መኝታ ቤቶች ከ15 ሺህ እስከ 20 ሺህ፣ እንዲሁም ባለሶስት መኝታ አፓርታማዎች እስከ 28 ሺህ ብር እየተጠየቀባቸው መሆኑ ተመላክቷል። የዋጋ ንረቱ ከነዋሪዎች የገቢ አቅም ጋር ፍጹም እንደማይገናኝ የገለጹት ነዋሪዎች፣ የደላሎች ሕገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት እና የዋጋ ጭማሪ ችግሩን ይበልጥ እንዳባባሰው አስታውቀዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗