ሩሲያ እና ዩክሬን በአሜሪካ አደራዳሪነት የሰላም ውይይት ጀመሩ

ADDIS_NEWSneutral2026-11-11 09:09:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሩሲያ እና ዩክሬን በአሜሪካ አደራዳሪነት የሰላም ውይይት ጀመሩ ለዓመታት የዘለቀውን የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ለመቋጨት ያለመ ከፍተኛ የሰላም ውይይት በአሜሪካ አደራዳሪነት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አቡዳቢ ከተማ መጀመሩ ተገልጿል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ ወገኖች ወደ ስምምነት ለመምጣት የሚያስችሉ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች መኖራቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪም ውይይቱ ገንቢ እና ጦርነቱን ለመቋጨት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን መናገራቸው ተመላክቷል። በመጀመሪያው ቀን ውይይት ተስፋ ሰጪ ፍንጮች ቢኖሩም፣ በግዛት ወሰን፣ በወደፊት የደህንነት ዋስትናዎች እና በኔቶ መስፋፋት ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት አሁንም ድረስ ጉልህ የሀሳብ ልዩነቶች እንዳሉባቸው ተጠቁሟል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]