የእሬት መድኃኒትነት እና የምርት መጠን ከሚበቅልበት ቦታ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት እንዳለው አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ።
የእሬት መድኃኒትነት እና የምርት መጠን ከሚበቅልበት ቦታ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት እንዳለው አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ። 🇪🇹 በኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች በሰሜን ሸዋ ዞን በተካሄደው ጥናት፣ የእሬት ተክል የሚበቅልበት ወረዳ እና ዝርያው ተክሉ የሚኖረውን የመድኃኒትነት ይዘት፣ የማዕድናት መጠን እና የቅጠል ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚወስነው ተረጋግጧል። ዋና ዋና መረጃዎች 🟠 የተጠኑ አካባቢዎች (3 ወረዳዎች)፦ ከአንኮበር፣ ከመርሃቤቴ እና ከከዎት የተሰበሰቡ 6 የተለያዩ የእሬት ዝርያዎች በጋራ አንድ ቦታ ተተክለው ተመዝግበዋል። 🟠የከዎት እና የአንኮበር የእሬት ዝርያዎች ከፍተኛ የመድኃኒትነት ይዘት፣ የማዕድን ስብጥር እና ከፍተኛ የቅጠል ምርት በማስመዝገብ በግንባር ቀደምነት ተለይተዋል። 🟠 ጥናቱ አርሶ አደሮች ተክሉን "ወንዴ" እና "ሴቴ" እሬት ብለው የሚለዩበትን ባህላዊ እውቀት…
Read the full story at addis_news ↗