ግምታዊ ዋጋቸው 4.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ግምታዊ ዋጋቸው 4.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ ህገ-ወጥ መድኃኒቶቹ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆናቸውን የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ጊኒር ከተማ ፖሊስ አስታውቋል ። የጊኒር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኢንስፔክተር አቡበከር ኢብራሂም እንደገለጹት፤ መድኃኒቶቹ በከተማው ውስጥ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችተው እያሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል። እነዚህ መድኃኒቶች መነሻቸውን ከሶማሌ ክልል ቀብሪደሃር እና ጅጅጋ አድርገው ጊኒር ከተማ በመግባት፣ አንድ ሙሉ መኖሪያ ቤት በመከራየት የተከማቹ ናቸው። ከተማውን እንደ ማከማቻ ማዕከል በመጠቀምም ወደ አዳማ፣ ሮቤ፣ ሻሸመኔ፣ አሰላ እና አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ የተለያዩ ከተሞች ሲያከፋፍሉ እንደነበር በማስረጃ መረጋገጡን ሐላፊው…
Read the full story at zena24now ↗