የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አድርገዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አድርገዋል። ሚኒስትሩ የተማሪዎች ማደሪያዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከተቋሙ ሦስት ካምፓሶች መምህራን እና ተማሪዎች ጋር በአገራዊ የትምህርት ሪፎርሞች ላይ ውይይት አካሒደዋል። ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከሦስት ዓመት በፊት ከነበረበት ሁኔታ አሁን ላይ የሚታየው ለውጥ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማኅበረሰቡን ኑሮ በጥናትና ምርምር በመደገፍ ማሻሻል እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል። @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗