#COP31

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-11-11 16:00:29 UTC
AdYour ad here[email protected]

#COP31 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቱርክዬ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ አሁን ላይ ከቃል ኪዳን ባለፈ በቀላሉ ተደራሽ በሆነ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችና በተጋላጭ ማኅበረሰቦች የመቋቋም አቅም ግንባታ ላይ ወደ ፈጣን ተግባራዊ እርምጃ መሸጋገር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። " ኢትዮጵያ በመደመር ፍልስፍና እየተመራች በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ተክላለች እንዲሁም የታዳሽ ኃይል ልማትንና ዘላቂ የከተማ ግንባታን በስፋት እያሳደገች ነው " ሲሉ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ መጪውን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ስትረከብ እነዚህን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች በግንባር ቀደምትነት እንደምታራምድና መላውን ዓለም ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]