👮‍♂️ትራፊክ ፖሊስ ፤ አሽከርካሪን ገደለ❗️

BROOK_NEWS_ETHIOPIAneutral2026-11-11 16:40:08 UTC
AdYour ad here[email protected]

👮‍♂️ትራፊክ ፖሊስ ፤ አሽከርካሪን ገደለ❗️ 👮‍♂️በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በደብረ ታቦር ከተማ "ቄስ ዓለማየሁ" በሚባል አካባቢ ትናንት ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. አንድ አሽከርካሪን "ሕግ ጥሰሃል" በሚል ምክንያት በትራፊክ ፖሊስ መገደሉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። አስተያየታቸውን የሰጡት ነዋሪዎች፤ የትራፊክ ፖሊስ አባሉ አሽከርካሪውን ከሚያሽከረክረው መኪና ላይ ካወረደው በኋላ በመሳሪያ ሰደፍ ጭንቅላቱን በመምታት ሕይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል ብለዋል። 👮‍♂️ወንጀሉን ፈጽሞ ከአካባቢው ተሰወሮ የነበረው የፖሊስ አባል ዛሬ ጠዋት በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋሉን ነዋሪዎች ጨምረው ገልጸዋል። ጉዳዩን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለደብረ ታቦር ከተማ የፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር ያለዉ በስልክ ለመገናኘት ጥረት የተደረገ ቢሆንም፣ በስልክ ሊገኙ አልቻሉም። Via DW

Read the full story at brook_news_ethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]