ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ያጣችውን የባህር በር ለማስመለስ የጀመረችው ጉዞ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ያጣችውን የባህር በር ለማስመለስ የጀመረችው ጉዞ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በሯን ለማስመለስ የጀመረችው ጉዞ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት የኢትዮጵያ አረጋውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ክፍሉ ናቸው። ውይይትና ዲፕሎማሲያዊ መንገድን ባስቀደመ መልኩ ቀይ ባህርን ለማስመለስ የተሄደበት ርቀት ዘመኑን የሚዋጅ ነው ብለዋል። የቀደመው አመራር ቀይ ባህርን በታሪክ አጋጣሚ ለሌሎች ሀገራት አሳልፎ መስጠቱን አንስተው፣ የኢትዮጵያን የቀደመ የባለቤትነት ታሪክ መመለስ የሚገባው በሰላማዊ የዲፕሎማሲ መንገድ መሆን አለበት ብለዋል። አረጋውያን አሁን ላለው ትውልድ ጥያቄዎችን በስክነትና በተረጋጋ መንፈስ በሚደረግ ድርድርና ውይይት ማስመለስ እንደሚቻል የማስተማር ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።…
Read the full story at addis_news ↗