ካሜራ መግጠም ተጀመረ‼️
ካሜራ መግጠም ተጀመረ‼️ የገቢዎች ሚኒስቴር የኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ የሆኑ የማምረቻ ተቋማት፣ በተለይም የቢራና የታሸጉ መጠጦች ፋብሪካዎች ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የክትትል ካሜራዎችን መግጠም መጀመሩ ታወቀ። መንግሥት ለዲጂታል የክትትል ሥርዓቱ ወደ 300 ሚሊዮን ብር የሚገመት በጀት መድቧል። ካሜራዎቹ የምርት መስመሮችን፣ የማሸጊያ ክፍሎችን፣ መጋዘኖችን፣ የጭነት መውጫዎችንና የምርት መጓጓዣን በቅጽበት ለመከታተል እንደሚውሉ ተገልጿል። ሥርዓቱም የፋብሪካዎች ትክክለኛ ምርት ከሚያሳውቁት የምርት መጠን ጋር ያለውን ልዩነት በመቆጣጠር የግብር ማምለጫን ለመቀነስ ያለመ ነው። በመመሪያዎቹ መሠረት አልኮል፣ ቢራ፣ ወይን፣ የታሸገ ውሃ፣ ትምባሆ፣ ሽቶ እና ጣፋጭ ወይም ካርቦኔትድ መጠጦችን ጨምሮ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ምርቶች በዲጂታል ኮድ ወይም በኤክሳይዝ ማህተም እንዲለዩ ይደረጋል።…
Read the full story at addis_reporter ↗