"ለበዓል በይቅርታ የሚፈታ ታራሚ የለም" — የፍትህ ሚኒስቴር
"ለበዓል በይቅርታ የሚፈታ ታራሚ የለም" — የፍትህ ሚኒስቴር አዲስ ዓመትንና ሌሎች በዓላትን ምክንያት በማድረግ በይቅርታ የሚፈታ ታራሚ አለመኖሩን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የማረምና ማነጽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ጽጌ የማነ ለመነኻሪያ ሬዲዬ እንደገለጹት፤ አሁን ላይ ለታራሚዎች ይቅርታ የሚደረገው አዲሱን መመሪያ መሠረት በማድረግ በቦርድ ሲወሰን ብቻ ነው። አብዛኛው ሰው ይቅርታን እና ምህረትን እንደሚያመሳስላቸው የጠቀሱት ዳይሬክተሯ፣ ምህረት በመንግሥት ጣልቃ-ገብነት ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ የሚፈልግ መሆኑን አብራርተዋል። ይሁን እንጂ በክልሎች በኩል በልዩ ሁኔታ በርዕሳነ-መስተዳድሮች እና በቦርድ አማካኝነት በአዲስ ዓመት በምህረት የሚለቀቁ ታራሚዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። #WasuMohammed 👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇…
Read the full story at wasulife ↗