ለጋብቻ ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል ፍቅረኛውን የገደለው ግለሰብ ተያዘ
ለጋብቻ ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል ፍቅረኛውን የገደለው ግለሰብ ተያዘ በሰሜን ቤንች ወረዳ ቃሻ ቀበሌ ሳድንስ መንደር ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው። ተከሳሽ ፍቃዱ ግሽናብ የተባለ ሲሆን ከተበዳይ ጋር ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ ይተዋወቁ እንደነበርና በኋላም የፍቅር ግንኙነት መስርተው እንደነበር ተገልጿል። በ2016 ዓ.ም ተከሳሹ የተበዳይን ፈቃድ ሳያገኝ ለማግባት በማሰብ የጠለፋ ወንጀል ይፈፅማል። ተበዳይዋ ወደፊት ከተከሳሹ ጋር ለመጋባት ፈቃደኛ አለመሆኗንና ሌላ የፍቅር ግንኙነት መጀመሯን ተከትሎ ተከሳሹ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያወጣውን ገንዘብ በማመካኘት በተበዳይዋ ላይ ቂም ይዞ መቆየቱ ተነግሯል፡፡ በዚህም ምክኒያት የግድያ ወንጀሉን እንደፈጸመ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡ ተከሳሹ ወንጀሉን ከፈጸመ…
Read the full story at addis_reporter ↗