በሆሳዕና በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ
በሆሳዕና በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ ዛሬ ከቀኑ 9:50 ላይ ከሆሳዕና ወደ ማዞሪያ ሲጓዝ የነበረ "ኮድ 3-24200 ደ.ህ" አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በቃጫ ቢራ ወረዳ ሚኖ ቀበሌ "ታችኛው ዋዶሌ" አካባቢ በፍሬን ችግር ተገልብጦ የአስከፊ አደጋ ሰለባ ሆኗል። በአደጋው የሰባት ወንዶች ሕይወት ሲያልፍ፣ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። አራት ከባድ እና ሁለት ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በአሁን ሰዓት በሺንሽቾ እና በዱራሜ ሆስፒታሎች የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። የወረዳው ትራፊክ ፖሊስ አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ ቴክኒክን ቅድመ ዝግጅት እንዲያረጋግጡ እና አደጋ በሚበዛበት በዚህ ስፍራ ልዩ ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያሽከረክሩ አሳስቧል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗