ታሪካዊው ዲአፍሪክ ሆቴል በሐራጅ ሊሸጥ ነው
ታሪካዊው ዲአፍሪክ ሆቴል በሐራጅ ሊሸጥ ነው ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ሲጎተት የቆየውን የውርስ ክስ እልባት ለመስጠት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ታሪካዊውን ዲ አፍሪክ ሆቴል በመጪው መስከረም ወር በሐራጅ ተሸጦ እንዲካፈል ውሳኔ መተላለፉን ከፎርቹን ጋዜጣ ሰምተናል። ባለ ስድስት ፎቁ ሆቴል የቦታው መስራች በሆኑት በአቶ ሰይፉ ገብረዮሐንስ ወራሾች መካከል በአይነት ተከፋፍሎ ሊደርስ ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ንብረቱን በሐራጅ መሸጥን እንደ የመጨረሻ አማራጭ ለመውሰድ መገደዱ ተገልጿል። በሜክሲኮ አደባባይ አቅራቢያ በ3,793 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈው ይህ ሆቴል፣ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ጀምሮ የአህጉሪቱን መሪዎችና እንግዶችን ያስተናገደ ታሪካዊ ቅርስ መሆኑ ይታወቃል። ፍርድ ቤቱ ለሐራጁ መነሻ የሚሆን ዋጋ ወደ 184 ሚሊዮን ብር ገደማ የተተመነ ቢሆንም…
Read the full story at addis_news ↗